ዓላማ
ይህ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምላሽ ለማጣቀሻነት የሚከተሉትን ዋና ዋና ጉዳዮች ያካትታል
- የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የሚያከናውኑትን ዝርዝር ተግባራት
- ለኮቪድ 19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱ የጥንቃቄ እርምጃዎች እና ቁልፍ መልዕክቶችን
- የመተንፈሻ አካላት ህመም ምልክቶች ልየታና የሚወሰዱ አስፈላጊ እርምጃዎችን
- የኮቪድ 19 ክትባት አሰጣጥ ግዜ የሚኖራቸውን ሚና እና ኃላፊነት
- የኮቪድ 19 የቤት ውስጥ ልየታ እና ክብካቤ/ክትትል አሰጣጥ መርሆችን ማስገንዘብ
- የተቀናጀ መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጊዜ ማስቀጠል
ከዚህ በተጨማሪ የኮቪድ 19 መሰረታዊ መረጃዎችን የሚተነትን፤ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ራሳቸውን ከኮሮና ቫይረስ እንዴት አንደሚከላከሉ የሚገልጽ፤ መድሎና መገለል መከላከልን በተመለከተ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማጣቀሻ አንዲሆን የተዘጋጀ ነው፡፡