ማጣቀሻው የሚከተሉት ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፡-
- የኮቪድ 19 መሰረታዊ መረጃ
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማወቅ ያለባቸው የኮቪድ 19 በሽታ መሰረታዊ መረጃዎችን፤ ራስን ከኮቪድ 19 በሽታ እንዴት መጠበቅ እንዳለብን፤ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችና የልማት ቡድን መሪዎች ተግባርና ሃላፊነቶችን የሚያመላክት ክፍል ነው፡፡
- የኮቪድ 19 ክትባት መረጃ
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማወቅ ያለባቸውን የኮቪድ 19 ክትባት መሰረታዊ መረጃ እና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ክትባትን በማዳረስ ሂደት ውስጥ ያላቸውን ሚና የሚያመለክት ክፍል ነው፡፡
- የኮቪድ 19 መሰረታዊ ህክምና አገልግሎት መረጃ
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማወቅ ያለባቸውን ምርመራ፤ ልየታ፤ የታማሚ ቅብብሎሽ እና መሰረታዊ ህክምና አገልግሎት እንዲሁም የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከዚህ አንጻር ያለባቸውን ሀላፊነት የሚመለከት ክፍል ነው፡፡
- የቤት ለቤት፤ የስራ ቦታ እና ተቋማት ዳሰሳ
የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የቤት ለቤት፤ የስራ ቦታ እና ተቋማት ዳሰሳ ሲያካሂዱ የሚጠቀሙበት ማጣቀሻ የያዘ ክፍል ነው፡፡