ኮቪድ 19 ምንድን ነው?
- ኮቪድ 19 ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡
- ይህ በሽታ እንደ ጉንፋን መሰል ምልክቶችን አሳይቶ በራሱ ሊድን ወይም ተባብሶ እንደሳንባ ምች (pneumonia)፣ ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም እንዲሁም ሌሎች የሰውነት አካላት ስራዎችን በማስተጓጎል ሞትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
- ኮቪድ 19 እድሜ፣ ጾታ፣ ዘር፣ ቀለም ሳይለይ በፍጥነት በርካታ ሰዎችን የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡