የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶች

- መራራቅ፡- አለመጨባበጥ፣ አለመሳሳምና አለመተቃቀፍ ከማንኛውም ሰው ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ያህል መራቅ
- መታጠብ፡- እጅን በሳሙና/አመድና በውሃ ቶሎ ቶሎ በደንብ መታጠብ አሊያም አልኮል ባለው የጀርም ማጽጃ በማሸት ማጽዳት
- መሸፈን፡- የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ/ማስክ ማድረግ ፣ በሚያስሉበት እ ና በሚያስነጥሱበት ጊዜ አፍና አፍንጫን በታጠፈ ክንድ ወይም በሶፍት መሸፈን። የተጠቀሙበትን ሶፍትም ክዳን ባለው ዕቃ በአግባቡ ማስወገድ፣ የተጠቀሙበትን የእጅ ማህረም በተደጋጋሚ በሳሙናና ውሃ በማጠብ መጠቀም
- መቆየት፡- በማህበረሰብ ደረጃ ከፍተኛ የኮቪድ 19 ስርጭት በሚከሰትበት ጊዜ መውጣት በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር በቤት ውስጥ መቆየት፣በሚወጡበት ጊዜ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ (ማስክ መጠቀም)፤ሰዎች በሚሰባሰቡባቸው ቦታዎች አለመገኘት፣ አላስፈላጊ ጉዞዎች መቀነስ)
- መከተብ፦ የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ከማሳድአጉም በላይ በበሽታው ምክኒያት ሊመጣ የሚችለውን የከፋ ህመምና ሞት ይከላከላል