የኮቪድ 19 በሽታ መከላከል ላይ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ዋና ዋና ሚና

- ህብረተሰቡ ውስጥ ላሉ አደረጃጀቶች፣ ስለ የኮቪድ 19 በሽታ ምንነት፣ የመተላለፊያ እና የመከላከያ መንገዶች ማስገንዘብ
- በህብረተሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎችን፣ በመለየት ስየኮቪድ 19 በሽታ ማስገንዘብና በመከላከል ሥራው ላይ ማሳተፍ፤ እንዲሁም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ማሳተፍ

- ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸውን ጊዜያት እና ቦታዎች በመለየት የበሽታውን ስርጭት በሚቀንስበት መልኩ እንዲካሄድ ማስተማር
- ማህበረሰብ ተኮር የቤት ለቤት የመተንፈሻ አካል ህመም ቅኝትና አሰሳ ማካሄድ
- በህብረተሰቡ ውስጥ ስለ ኮቪድ 19 የሚነገሩ/የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን በመከታተል ትክክለኛውን መረጃ በመስጠት ማስተካከል

- በማህበረሰቡ የሚሰጡ አስተያየቶችን ወይም ጭምጭምታዎችን መለየት እና ለፈጣን ምላሽ ቡድን ወይም ለወረዳ ማሳወቅ
- በህብረተሰብ ደረጃ የወረርሽኙን ቅድመ ዝግጅት እና ምላሽ ስራዎች ማስተባበር