በስብሰባ ወቅት ሊተገበሩ የሚገቡ የጥንቃቄ እርምጃዎች ማስገንዘብ

‘‘ስብሰባ’’ ማለት ማንኛውንም ተግባር ለመፈጸም፣ ለመነጋገር፣ ስልጠና ለመስጠት፣ ለመወያየት፣ ግንዛቤ ለማስጨበጥ፣ ወይም መሰል ተግባራትን ለማከናወን የአንድ ቤተሰብ አባላት ከሆኑ ውጪ አራትና ከዚያ በላይ ሆኖ ከሁለት ሰዓት በላይ በቤት ዉስጥ ወይም ድንኳን በመሳሰሉ በተከለለ ሁኔታ በአካል መገኘት ማለት ሲሆን እንደ አግባብነቱ እንደ ሠርግ፣ ምርቃት፣ እና መሰል የማህበራዊ ዝግጅቶች ለማድረግ የሚደረግ መሰባሰብም ያጠቃልላል፡፡
በስብሰባ ወቅት የሚደረጉ ጥንቃቄዎች
- ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቆ መቀመጥ
- የእጅ ንጽህናን መጠበቅ
- የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ
- የቆይታ ጊዜን ማሳጠር
- ከቤት ውጪ አየር እንደ ልብ በሚዘዋወርበት ቦታ ስብሰባውን ማካሄድ
- የስብሰባ አዳራሹ/ቦታ የተለየ መግቢያ እና መውጫ በር እንዲኖረው ለማድረግ መሞከር

- በተደጋጋሚ ንክኪ የሚበዛባቸዉን ቦታዎች በፀረ ተህዋስያን ኬሚካል ማጽዳት/መወልወል
- በቂ የሆኑ ክዳን ያላቸዉ የቆሻሻ ማስወገጃ እንዲኖር ማድረግ
- በተቻለ መጠን ቁሳቁሶችን በጋራ አለመጠቀም
- የጥንቃቄ እርምጃዎችን የሚከታተል ሰዉ መመደብ