በለቅሶ ጊዜ ስለሚደረጉ ጥንቃቄዎች የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያ ማስተማሪያ
- ሟች ሲገለገልባቸው የነበሩ የግል ቁሳቁሶች በጸረ ተህዋሲያን ውህድ እንዲፀዳ ማስተማር
- ሞት ሲከሰት በአስክሬን ማስተካከልም ሆነ ግነዛ ሂደት ከሟች ቤተሰቦችም ሆነ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖሩ ማንኛውም ግንኙነቶች ወይም በቦታው የሚደረግ እንቅስቃሴ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በጠበቀ መልኩ መሆን እና አስክሬን የሚያስተካክሉና የሚገንዙ ሰዎች የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ፣ከፕላስቲክ የተሠራ ጋዋን ወይም ላስቲክ እንደ አስፈላጊነቱም የአይን መከላከያ ወይም መነጽር እንዲለብሱ ማስተማር
- የሟች ቤተሰብ ወይም ለሟች ኃላፊነት ያለበት ሰው አስከሬኑንም ሆነ አስክሬን ያለበትን ሳጥን ያለመነከካት ወይም ያለመሳም ፣ አስክሬን ያለበትን ሳጥን ወይም አስክሬን የተጫነበትን ሌላ እቃ በጸረ ተውሃሲያን ውህድ እንዲፀዳ ማስተማር
- የሟችን አስክሬን የሚገንዙ ሰዎች የአስክሬን ማስተካከሉና መገነዝ ሂደቱ ካጠናቀቁ በኋላ የተጠቀሙበትን የእጅ ጓንት፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እና ሰውነታቸውን የሸፈኑበትን ፕላስቲክ ወይም ጋዎን በአግባቡ የማስወገድ እና እጆቻቸውን በውሃ እና በሳሙና እንዲታጠቡ ማስተማር
- በለቅሶ ቦታ የተገኘ ማንኛውም ሰው ተገቢውን የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲያደርጉ መምከር