ከቀብር ስነ-ስርአት በኋላ የሚኖሩ ግዴታዎች

- ከቀብር በኋላ ለቅሶ መቀመጥ በድንኳን፣ በቤት ውስጥ ወይም ለዚሁ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ሲደረግ ሀዘንተኛው እና የቤተሰቡ አባላት እና ለቅሶ የሚደርሰው ሰው ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀትን በመጠበቅና ባለመነካካት እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ እንዲያደርጉ ማስተማር

- በለቅሶ እና በቀብር ስርአት በኋላ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመነካካት ወይም ሊያነካካ በሚችል መልኩ መመገብ፣ ወይም በሌሎች ሰዎች በተነካኩና ባልታጠቡ እቃዎች እንዳይመገቡ ማስተማር
- ማንኛውም ለቅሶ ሊደርስ የመጣ ሰው ወደ ለቅሶ ቤት ከመግባቱ በፊትና ከለቅሶ ቤት ሲወጣ እጁን በውሃና ሳሙና የመታጠብ ወይም በሳኒታይዘር የማፅዳት ግዴታ እንዳለበት ማስተማር