በኮቪድ-19 መከላከል ዙሪያ የልማት ቡድን መሪዎች ተግባራት
- ከጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በሚያገኙት የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰረት
- ለቤተሰባቸውና የልማት ቡድን አባላት ስለ ኮቪድ19 ምንነት፣ የመተላለፊያና የመከላከያ መንገዶች ማስገንዘብና መተገበር
- በህብረተሰቡ ውስጥ ስለ ኮቪድ 19 የሚነገሩ የተሳሳቱ ሃሳቦችን ለማስተካከል ትክክለኛውን መረጃ መስጠትና ጭምጭምታዎችን ማሳወቅ
- በሚኖሩበት መንደር/ጎጥ የመተንፈሻ አካል ህመምተኛ ሰው ወይም ከህመምተኛ ጋር ንክኪ ያለው ሰው ሲያጋጥም ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማሳወቅ
- በበሽታው ተጠርጣሪ የሆነ ወይም ከህመምተኛ ሰው ጋር የቅርብ ንክኪ ያለው/ያላቸው ሰው/ሰዎች በማህበረሰቡ መገለል እንዳይደርስባቸው በማህበረሰቡ ዘንድ የሚከሰቱ የተዛቡ ግንዛቤዎችን ማስተካከል
- በህብረተሰቡ ውስጥ በብዛት ሰዉ የሚሰበሰብባቸዉን ጊዜያት እና ቦታዎች መለየት (የንግስ በዓላት፣ ሰንበቴ፣ ጁምዓ፣ አምልኮ፣ ጸበል፣ ት/ቤት...) እና ስለ ኮቪድ 19 መረጃ መስጠት/ግንዛቤ ማስጨበጥ
- ባልተለመደ ሁኔታ በአንድ አካባቢ በርከት ያለ ሰው በትኩሳት፣ በሳል አንዲሁም በመተንፈስ ችግር የሚከሰት ሞት ካለ በአፋጣኝ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ሪፖርት ማድረግ