የኮቪድ 19 ክትባት አተገባበር
4.1.1 የኮቪድ 19 ክትባት
- የኮቪድ 19 ክትባት የሰውነት መከላከያ አቅምን በማነሳሳት የኮቪድ 19 አምጪ ቫይረስን በመዋጋት ከበሽታው ይከላከላል
- የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም ከማሳድጉም በላይ በበሽታው ምክኒያት ሊመጣ የሚችለውን የከፋ ህመምና ሞት ይከላከላል
- የኮቪድ 19 ክትባት ከወሰዱ ከሁለት ሳምንታት በኋላ የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን ይጨምራል
- በዓለም ላይ የተለያዩ የኮቪድ 19 ክትባት አይነቶች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም ዓይነት ክትባቶች የከፋ የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያመጡ በአለም የጤና ድርጅት ተፈትሸው ብቃታቸው ተረጋግጦ የሚሰጡ ናቸው።