የኮቪድ 19 ክትባትን በማህበረሰቡ ውስጥ ማስረጽ
- ህብረተሰቡ ሊረዳው በሚችለው ሁኔታ ፖስተሮችን እና የተለያዩ ምስሎችን በመጠቀም ቀጣይ በሆነ መልኩ ስለ ኮቪድ 19 ክትባት ማስተማር
- የኮቪድ 19 ማስተማሪያ ፖስተሮችን እና የተለያዩ ምስሎችን ለህብረተሰቡ ጎልተው በሚታዩ ቦታዎች መስቀል/መለጠፍ
- በወረዳ ውስጥ ያሉ አመራሮች እና የሃይማኖት አባቶች ስለኮቪድ 19 ክትባት ለማህበረሰቡ አርአያ በመሆን እንዲያስተምሩ ማድርግ
- የኮቪድ 19 ክትባት ዘመቻ ላይ መሳተፍ
- የማህበረሰብ ንቅናቄ መስራት
- ከክትባቱ ጋር የተያያዘ የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸውን ሰዎች መለየት
- ከጤና ጣቢያ ጋር በመቀናጀት የክትባት አሰጣጥ ሂደቱን ማስተባበር
- የጤና ሚኒስቴር በሚያውጣው የኮቪድ-19 ክትባት መመሪያ መሰረት ታላሚ የማህበረሰብ ክፍሎችን መለየት
- ተከታቢዎችን በጎጥ በመለየት የክትባት መስጫ ቦታና ጊዜ በማሳወቅ ለልማት ቡድኖች እንዲቀሰቅሱ ማድረግ።
- ለተለያዩ አደረጃጀቶች ስለክትባቱ ጥቅም ግንዛቤ ማስጨበጥ።
- በክትባት ዙሪያ ላይ የማህበረሰብ ውይይት ማካሄድ።