ጥያቄዎች: የኮቪድ-19 በሽታ ክትባት ጥቅሙ ምንድን ነው? መልስ
የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት የሰውነትን በሽታ የመከላከል አቅም በማሳደግ ሰው እንዳይያዝ ከመከላከሉም በላይ ቢያዝ እንኳን አደገኛ ከሆነ ህመም እና ሞትን ይከላከላል |
ጥያቄዎች: ክትባቱን እጠራጠረዋለሁ መልስ
የክትባቱ የኮቪድ -19 በሽታን ለመከላከል የተዘጋጀ መድህኒት ነው ልክ እንደሌሎቹ ክትባቶች |
ጥያቄዎች: የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ ክትባት የሚሰጠው ለማን ነው? መልስ
የጤና ሚኒስቴር ባስቀመጠው መስፈርት መሰረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰዎቸ ክትባቱን ያገኛሉ |
ጥያቄዎች: ክትባቱን ስወስድ የሚያመኝ ይመስለኛል መልስ
ክትባቱ እንደማንኛውም መድህኒት ቀላል የጎዮሽ ችግሮች አሉት እነዚህ ችግሮች በጥቂት ቀናት ውስጥ የሚጠፉ ናቸው |
ጥያቄዎች: ክትባቱን ከተከተብኩ ማስክ አላደርግም? መልስ
አይ! ክትባቱ ውጤታማ የሚሆነው ከሌሎቹ የኮቪድ-19 በሽታ መከላከያ መንገዶች ጋር ነው፡፡ ስለዚህ ብንከተብም ባንከተብም ርቀትን መጠበቅ፣ እጅን በውሀና ሳሙና መታጠብ ወይም ሳኒታይዘር መጠቀም እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ/ጭምብል መጠቀም መቀጠል ይኖረባቸዋል |