የኮቪድ 19 መሰረታዊ ህክምና

- ኮቪድ 19 ህመምተኛ ያለበትን የህመም ደረጃ መለየት፤
- ምልክት የሌለው እና መለስተኛ ምልክት ያለውን እንዲሁም ምንም አይነት የታወቀ ተጓዳኝ ህምም የሌለው ታካሚ በቤት ውስጥ ክትትል ማድረግ፤
- መካከለኛ የኮቪድ 19 ህመምና የሳምባ ምች ያለበት ታካሚ በቤት ውስጥ ህክምና ከማግኘቱ በፊት በአቅራቢያዉ ባለ የጤና ተቋም ምርመራና ህክምና ማግኘት ይገባዋል፤
- የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛ ከጤና ተቋም ያገገመን እንዲሁም በቤት ውስጥ ልየታና ክብካቤ የተወሰነለትን ታካሚ ክትትል ማድረግ ይኖርባታል፤
- ኮቪድ 19 ታካሚ ለሚያሳያቸው ምልክቶች ማስታገሻዎች መስጠት ያስፈልጋል፤
- ትኩሳት እና ቁርትማት ላለው ታካሚ ፓራሲታሞል መስጠት ተገቢ ነው፤
- የድካም ስሜት ላላቸው ሰዎች 40 % ጉልኮስ መስጠት (የጉሉኮስ መጠናቸዉ ታዉቆ)፤
- በቤት ውስጥ ህክምና ላይ ያለን ታማሚ በቂ ምግብና ፈሳሽ እንዲወስድ፣ ቀለል ያለ አካላዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ፤