የኮቪድ 19 የቤት ውስጥ ክብካቤ/ክትትል አሰጣጥ

- ይህን አገልግሎት የሚያገኙ ሰዎች የኮቪድ 19 ቫይረስ እንዳለባቸዉ የተረጋገጠ ሆኖ የህመሙ ስሜቶች እና ምልክቶች የሌላቸው ወይንም መጠነኛ እና መካከለኛ ምልክት ያላቸው ናቸው፡፡
- እንዲሁም እድሜያቸው ከ60 አመት በታች እና ተጓዳኝ በሽታዎች (እንደ ስኳር በሽታ፤ የደም ግፊት፤ አስም፣ የቆየ የሳንባ በሽታ የመሳሰሉት) የሌለባቸው ታማሚዎች ናቸው፡፡
5.3.1 ከባድ ያልሆነ የኮቪድ 19 ህመም የሚባሉት እነማን ናቸው?
- ምልክት የማያሳይ የኮቪድ 19 ህመም
- መጠነኛ የኮቪድ 19 ህመም፡- እንደ ጉንፋን፣ ሳል፣ ትኩሳት፣ ድካም፣ መቅመስ እና ማሽተት መቀነስ/አለመቻል የሚያሳዩ
- መካከለኛ የኮቪድ 19 ህመም፡- የሳንባ ምች ምልክት ያላቸው(እንደ ሳል፣ ትኩሳት፣ የትንፋሽ ማጠር፣ ቶሎ ቶሎ መተንፈስ የመሳሰሉት) ወይም የኦክስጅን መጠናቸው ከ 90% በላይ የሆነ ህመምተኞች
5.3.2 ከባድ የሆነ የኮቪድ 19 ህመም
- ከባድ የሆነ የኮቪድ 19 ህመም ፡- ራስን አለመቆጣጠር/ ራስን መሳት፣ ፈጣን አተነፋፈስ መኖር፣ ማቃሰት፣ የኦክስጅን መጠናቸው ከ90% በታች የሆኑ ህመምተኞች