የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በኮቪድ 19 በቤት ውስጥ ልየታ እና ክብካቤ/ክትትል ላይ ያላቸው ተግባር እና ሃላፊነት

- ለቤት ውስጥ ክብካቤናክትትል የሚከተሉት መስፈርቶች መሟላታቸዉን ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ ቤት ውስጥ በሚቆይበት ጊዜያቶች ተንከባካቢ/አስታማሚ መኖሩን ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ በቤት ውስጥ የሚያስታምመው/የሚንከባከበው ሰው ከሌለ፤ ለሚቆይባቸው ጊዜያት አስፍላጊውን የምግብ እና ውሃ አቅርቦት መኖር እንዳለበት ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ ራሱን ለብቻው ለይቶ የሚያቆይበትን ክፍል ወይም ከሌለው የቤተሰብ አባል በ2 ሜትር ርቀት ለይቶ የሚያቆይበት እና በቂ የአየር ዝዉዉር ያለዉ መሆኑን ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ የመጸዳጃ እና ማብሰያ ቦታዎችን ከሌላው የቤተሰብ አባል ጋር በጋራ የሚጠቀም ከሆነ ታማሚው በተጠቀመ በኃላ በአግባቡ መጽዳት እንዳለበት ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ በቤት ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜያት ለቤት ውስጥ የሚፈጸም ጥቃት ወይም ትንኮሳ ተጋላጭ እንዳልሆኑ ማረጋገጥ
- በቤት ውስጥ በሽታውን ለመከላከል የሚጠቅሙ በቂ የሆነ የሰዉነት መከላከያ ቁሳቁስ (ማስክ፣ ጓንት ወዘተ)፣ የጽዳት ግብዓቶች(ሳሙና/አመድ፣ ውሃ እና በረኪና )መኖራቸዉን ና በአግባቡ መጠቀም መቻላቸዉን ማረጋገጥ
- ታማሚው/ዋ እና አስታማሚው የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ በሁሉም ጊዜ ማድረግ እንዳለባቸው ማረጋገጥ
- ስለ ቤት ውስጥ ልየታ እና እንክብካቤ ከታማሚ፣ ከአስታማሚ እና ከታማሚ ቤተሰብ ጋር መወያየት
- ህመምተኛውን፣ አስታማሚዉን፣ ቤተሰቡን እና ጎረቤቶቹን አጠቃላይ የኮቪድ 19 መከላከያ መንገዶችን ማስተማር
- የታማሚውን የጤና ሁኔታ መከታተል
- መካከለኛ የኮቪድ 19 ህመም ያላቸውን ታካሚዎች በየቀኑ በስልክ መከታተል
- በአካል ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታማሚዎች በክትትል ቡድኑ በሚወሰነው መሰረት መከታተል
- መጠነኛ ምልክት ላላቸው የኮቪድ 19 ህመምተኞች በየሶስት ቀኑ በስልክ ክትትል ማድረግ
- ምልክት ለማያሳዩ የኮቪድ 19 ህመምተኞች ሁለት ጊዜ በስልክ ክትትል ማድረግ
- የስልክ አገልግሎት በሌለባቸው ቦታዎች በአካል ክትትል ማድረግ
- ለህመምተኛው የቅርብ ክትትል የሚያደርገውን የቤተሰብ አባል ሪፖርት እንዲያደርግ ማድረግ
- የታማሚዎች የኦክስጅን መጠንን በኦክስጅን መጠን መለኪያ መሳሪያ መለካት
- በጤና ጣቢያ ላለው ለፈጣን ምላሽ ቡድኑ የህመምተኛውን የጤና ሁኔታ ማሳወቅ (የሪፖርት ጊዜዉ ይጠቀስ)
- ከባድ ህመም ያላቸውን ወይም ህመሙ የተባባሰባቸውን ህመምተኞችን በአቅራቢያ ወዳለው የጤና ተቋም ካሳወቁ በኋላ መላክ
- ተጋላጭ/ልዩ ክትትል የሚያስፈልጋቸው የቤተሰብ አባላት ያላቸውን ታማሚዎች ትኩረት ሰጥቶ መከታተል (ለምሳሌ፡- እድሜአቸው ከ60 አመት በላይ የሆኑ፣ ከሁለት አመት በታች የሆኑ፣ ነፍሰጡር እናቶች እና ሌሎች በሽታዎች (ስኳር በሽታ፣ ደም ግፊት፣ አስም፣ ካንሰር፣ የቆየ የሳንባ በሽታ የመሳሰሉት