በቤት ውስጥ ልየታ እና እንክብካቤ ጊዜ ለኮቪድ 19 ታማሚዎች የሚሰጥ የጥንቃቄ ትምህርቶች

- ከቤተሰብ አባላት እና ከተንከባካቢዎች ጋር ማንኛውንም አይነት ንክኪ ማስወገድ
- በቤት ውስጥ ራስን ለይቶ በትንሹ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከቤት አለመውጣት
- በቂ የአየር ዝውውር ባለበት ቦታ መቆየት
- የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛን/ማስክ (Medical mask) በአግባቡ ማድረግ፣ በየቀኑ ማስክን ከተጠቀሙ በኋላ በአግባቡ ማስወገድ እንዲሁም ሲረጥብ/ሲቀደድ በአዲስ መቀየር
- እጅን በውሃ እና በሳሙና/አመድ አዘውትሮ መታጠብ ወይም አልኮል ባለዉ የእጅ ማጽጃ መጠቀም
- የመመገቢያ እና የመጠጫ እቃዎችን መለየት፣ በሳሙና እና ውሃ፣ በረኪና ባለዉ ዉህድ (1 እጅ በረኪና ዘጠኝ እጅ ዉሃ) በማጽዳት ማለቅለቅ
- ከታማሚው የሚወጡ መወገድ ያለባቸው የምግብ ትርፍራፊዎች እና ሌሎች ቆሻሻዎችን በአግባቡ ማስወገድ

- አስቸኳይ የህክምና እርዳታ የሚሹ አደገኛ የሆኑ የኮቪድ 19 ምልክቶችን በየቀኑ እንዲከታተሉ ማስተማር (የሳል መባባስ፣ የደረት ውጋት፣ የትኩሳት መባባስ፣ የድካም መባባስ፣ የትንፋሽ ማጠር ፣ መዘባረቅ/አለመንቃት፣ ራስን አለመቆጣጠር፣ የከንፈር ቀለም መቀየር፣ የሽንት መጠን መቀነስ እና ቀለም መቀየር)