በቤት ውስጥ ልየታ እና ክብካቤ ጊዜ ለኮቪድ 19 ታማሚዎች የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ድጋፍ መስጠት

- ሰዎች አዕምሯዊ ጤንነታቸውን እና ስነ-አእምሮአዊና ማህበራዊ ደህንነታቸውን ለመጠበቅ የሚደረግ ማንኛውንም ድጋፍን ያጠቃልላል።
- በቤት ውስጥ ልይታና ክብካቤ ላይ ያሉ የኮቪድ 19 ታካሚሚዎች ከሚወዷቸው ሰዎች በመለየታቸው/በልየታው እንዲያዝኑ፣ብቸኝነት ወይም ችላ እንደተባሉ እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። በዛን ጊዜ የተለያዩ የስነ-ልቦና ምላሾች ልናይባቸው እንችላለን። ከእነሱም ዉስጥ የሚከተሉት በዋነኝነት ይጠቀሳሉ
- ግራ የሚያጋቡ ስሜቶች - ፍርሃት፣ ቁጣ፣ ሀዘን፣ እፎይታ
- ድብርት - ተስፋ መቁረጥ፣ በነገሮች ላይ ፍላጎት ማጣት፣ ብቸኝነትን መምረጥ
- ስለራሳቸው እና ስለወዳጆቻቸው ጤና መፍራት እና መጨነቅ
- ረጀም ሰዓት በቤት ውስጥ በመቆየታቸው የተነሳ የሚፈጠር ውጥረት
- ጓደኞቻቸው ወይም የሚወዷቸው ሰዎች በሽታውን አስተላለፍባቸዋለሁ ብሎ ከመፍራት የሚመጣ ብስጭት እና መጨናነቅ
- መደበኛ ሥራ ወይም የወላጅነት ተግባራትን ማከናወን ካለመቻል የሚመጣ የጥፋተኝነት ስሜት
- እንደገና እታመማለው ብሎ መጨነቅ ናቸው
- እነዚህ ምልክቶች የሚታይበት የኮቪድ 19 ታማሚ ግለሰብ የአዕምሮ ጤና እና ስነ-ልቦናዊ ማህበራዊ ድጋፍ ያስፍልገዋል። በዚያን ጊዜ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሞያዎች የሚከተሉትን ተግባራት በመሠረታዊነት ቢያደርጉ ይመከራል
- የስልክ ጥሪዎችን እና ተመሳሳይ መንገዶችን በመጠቀም ከቤተሰብና ከሌሎች ወዳጆቻቸው ጋር ያላቸውን ማህበራዊ ግንኙነት ማስቀጠል
- ራስን የመንከባከብ ስልቶችን ማስጨበጥ
- እንደየ አካባቢው የባህል እና የአኗኗር ዘይቤ ጤናን ሊጎዱ ከሚችሉ መጠጦችና ተግባራት ራሳቸውን እንዲያርቁ ሃሳብ መስጠት

- በግላቸው ሊያከናውኑ የሚችሉት መደበኛ የቤት ውስጥ ስራዎችን እንዲለዩ እና እንዲተገበሩ ማገዝ
- ከሬድዮ፣ ከቴሌቪዥን እና ሌሎች መገናኛ ብዙሃን ዘዴዎች የሚያገኙትን መረጃ መምረጥ፣ መወሰን፣ እንዲችሉ ማሳወቅ
- የአእምሮ ጤና እና ስነአእምሮአዊ ማህበራዊ ስጋት ላለባቸው ሰዎች ተጨማሪ ድጋፍ ወደሚሰጥ ጤና ተቅዋም ማገናኘት እና
- የሐይማኖት አባቶች መንፈሳዊ ድጋፍ እንዲሰጧቸው ሁኔታዎችን ማመቻቸት