ዓለሙ በምትሰሪበት የጤና ኬላ የሚኖር የ37 ዓመት ጎልማሳ ነው። ዓለሙ የደም ግፊት በሽታ ያለባቸውን የ53 አመት እድሜ ያላቸው እናቱን፣ የ69 ዓመት አዛውንት አባቱን፣ ከወንድሞቹ ከከተማ በሚላክለት ገንዘብ እና ከግብርና በእንስሳት እርባታ እና በእርሻ የሚያገኘውን እህል በመሸጥ እና ለእለት ከእለት ጥቅም በማዋል ያስተዳድራል። ኮቪድ-19 በሽታ ከገባ በሗላ ብርቅነሽን አግብቶ የ 1 ዓመት ከ3 ወር ልጅ አለው። የዛሬ ሶስት ቀን ትኩሳት ምልክት የነበረው ሲሆን፣ ከ6 ቀናት በፊት ገበያ በወጣበት ቀን ወደ ባንክ ቤት በመሄድ ወንድሞቹ ለቤተሰብ የላኩለትን ብር አውጥቷል።
ከዚህ በታች የሚገኙትን ጥያቄዎች ስለዓለሙ ምላሽ ስጡ