የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ማወቅ ያለባቸውን የኮቪድ 19 የሥርዓተ ምግብ መሰረታዊ መረጃ

- የተመጣጠኑ ምግቦችን መጥኖ መመገብ
- ከኮቪድ-19 በቶሎ ለማገገም ይረዳ ዘነድ ጤናማ የሆነ አመጋጋብ እንደ እህል፣ ጥራጥሬ፣የእንስሳት ተዋጽኦ እንደ ስጋ፣ እንቁላል፣ ወተት እና የወተት ተዋእጽኦ በተለይ አትክልት እና ፍራፍሬን አዘውትረው ይመገቡ ፤ ውሃ በቀን ከ 8-10 ብርጭቆ ይጠጡ፡፡
- ለሚያጠቡ እና እርጉዝ እናቶችን በተመለከተ
- በኮቪድ 19 የተያዘች እናት ጡት ማጥባት አያግድም!
- አፍና እፍንጫን በመሸፈን ፣እጅን በንፁህ ውሃ እና በሳሙና በመታጠብ ጡጥ ማጥባት መቀጠል ይኖርባታል ፡፡
- ነፍሰጡርና የሚያጠቡ እናቶች የራሳቸውንም ሆነ የልጃቸው ጤና ለመጠበቅ አቅማቸውን በፈቀደ የተመጣጠኑ ምግብ መመገብና ከዚህ በፊት ይመገቡት ከነበረው ተጨማሪ ከ1-2 ጊዜ መመገብ አለባቸው፡፡ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመጠበቅ የተለየ የአመጋገብ መመሪያ ስለሌለ በአገር አቀፍ ለእርጉዝ እና አጥቢ እናቶች የተዘጋጀ የአመጋገብ መመሪያን መከተል ያስፈልጋል፡፡
- የሃይማኖት አባቶችና በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያላቸው ሰዎች በኮቪድ -19 ለታመመ ሰው የስርዓተ-ምግብ አጠቃቀምን መምከር አለባቸው፡-
- የሃይማኖት አባቶች በኮቪድ -19 የተያዙ ሰዎችን በፍጥነት እንዲያገግሙ የሀኪም ምክር በመስማት አመጋገባቸውን ማስተካከል አለባቸው፡፡
- በኮቪድ-19 የታመሙ ሰዎች በፆም ወቅት የእንስሳትና የወተት ተዋፅኦዎችን መጠቀም ካለባቸው እንዲጠቀሙ በሃይማኖት አባቶች ምክር አገልግሎት ማግኘት አለባቸው፡፡
- በኮቪድ-19 የተያዙት ታማሚዎች በጭንቀት ምክንያት የምግብ ፍላጎታቸው ሊቀንስ ሰለሚችል መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል