በኮቪድ 19 እና ስርዓተ ምግብ ላይ በማህበረሰቡ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው


ጥያቄዎች VS. መልስ


ጥያቄዎች: ነጭ ሽንኩርት አብዝቶ መውሰድ ከኮቪድ-19 ለማገገም ይረዳል?

መልስ

ነጭ ሽንኩርት አብዝቶ መመገብ ከኮቪድ-19 ለማገገም ይረዳል የሚል መረጃ የለም፡፡

ጥያቄዎች: አልኮል መጠጣት ኮሮና ቫይረስ እንዳይዘን ይከላከላል?

መልስ

አልኮል መጠጣት ኮሮና ቫይረስ እንዳይዘን አይከላከልም፤ አልኮል የሚጠጡና የሚያጨሱ ሰዎች የበሸታ የመከላከል አቅማቸው ስለሚዳከምና ለከፋ የኮሮና ህመም ስለሚጋለጡ አልኮልንና ሲጋራን ከመጠቀም መቆጠብ፡፡

ጥያቄዎች: የሚያቃጥሉ ቅመማ-ቅመሞች መመገብ ከኮቪድ -19 በሽታ ይከላከላል?

መልስ

የሚያቃጥሉ ቅመማ-ቅመሞች መመገብ ከኮቪድ -19 በሽታ ከመከላከል ጋር ቀጥታ ግንኙነት የለውም