ቅድመ ዝግጅቶች

- ቅኝትና አሠሣ የሚያካሂደው ቡድን አሰሳውን የሚያካሄድበትን አካባቢ መለየት፤ ማካለል፤ በአካባቢው ያሉ የአባወራ/እማወራ እንዲሁም የተለያዩ ተቋማትን ብዛት መለየት
- የቡድኑ አባላትን ማንነትን የሚገልጽ መታውቂያ/ታግ ማድረግ፤ የጤና ባለሙያዎች ጋዋን መልበስ
- ጉብኝት የሚካሄድበትን አካባቢ ቤተሰብና ተቋማትን ብዛት መሰረት በማድረግ የመስክ ቡድን ማደራጀትና ዕለታዊ የስምሪት እቅድ ማዘጋጀት
- ለመስክ ስራ የሚረዱ ግባቶችን ማዘጋጀት
- የሰውነት ሙቀት መለኪያ፤
- የኦክስጅን መጠን መለኪያ መሳሪያ/ፐልስ ኦክሲሜትሪ
- ሳኒታይዘር እና 70% አልኮል
- የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፤ ሳኒታይዘር ጋዉን፣ ግላቭ
- መረጃ መሰብሰቢያ ሞባይል ስልክ/ታብሌት/ቅጽ፤
- የኮሮና ቫይረስ በሽታ ቁልፍ የጤና መልዕክቶች፤
- የማጣቀሻ መጽሐፍ፤
- መዝገብና መረጃ መሰብሰቢያ ቅጾች
- ባለፈው ዙር የተሞሉ ቅጾች
- መታወቂያ
- የቆሻሻ መሰብሰቢያ ፕላስቲክ (Biohazard Bag)