በቤት ለቤት ጉብኝት ወቅት መከናወን ያለባቸው ተግባራቶች

- ማንኛውም ቤት ሲገቡ በመጀመሪያ ለቤተሰቡ አባላት ሰላምታ አቅርቡ/እጅ ንሱ ነገር ግን በእጅ አትጨባበጡ
- በትህትና እራስዎንና የመስክ ቡድኑ አባላትን አስተዋውቁ፣ የቤት ለቤት ጉብኝቱ ዓላማ ምን እንደሆነ ለቤተሰቡ በተገቢ ሁኔታ ግለጹ/አስረዱ
- ማንኛውንም ትምህርት ከመስጠት በፊት በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ግንዛቤ ለዩ
- ጥያቄዎች ሲጠይቁ ግድ ካልሆነ ማብራሪያ የሚፈልጉ ጥያቄዎችን ይጠይቁ፤ ተገልጋዮች ሲናገሩ ለመረዳት ያዳምጡ የተረዳችሁትንም መልሶ በሌላ አገላለጽ ለተገልጋዩ በማስርዳት በተሳሳተ መንገድ አለመረዳታችሁን አርጋግጡ፣
- ተገልጋዩን በሚያዳምጡበትም ጊዜ ለምን የመከላከያ ተግባራቱን እየተገበሩ እንዳልሆነ ይለዩ፤ እስካሁን ለምን አልተገበሩም ብለው አይውቀሷቸው፣ ለመተግበር ያጋጠሟቸውን እንቅፋቶች እንደሚረዱ ይግለጹላቸው
- ተገልጋዮቹ እሚያነቃቃቸዉን በህይወታቸው የሚፈልጉት እና ቦታ የሚሰጡት ነገር ምን እንደሆነ ይለዩ
- የእውቀት ክፍተት ካለባቸው ለነሱ በሚመጥን ደረጃ ያስተምሯቸው፤ ተግባራዊ መፍትሄዎችን ከራሳቸው እንዲመጡ ያድርጉ ወይም መፍትሄ የሚጠይቁ ከሆነ የተለያዩ አማራጮችን አቅርበው እንዲመርጡ ያድርጉ
- ለመተግበር እንዲነሳሱም ተግባራቱን ከእሚያነቃቃቸዉ በህይወታቸው ከሚፈልጉት እና ቦታ ከሚሰጡት ነገር ጋር ያያይዙት
- አስፈላጊ ተግባራትን ለመተግበር ይችሉ ዘንድ ተገልጋዮቹ እችላለው ብለው በሚያስቡት ልክ እቅድ እንዲያቅዱ ይደግፏቸው
- እቅዱን ለመተግበር ያላቸውን ተነሳሽነት ይገምግሙ፣ አናሳ ከሆነ እቅዱን ይከልሱ፤ ተገልጋዩን በመተግበሩ የሚያገኛቸውን ከዚህ በፊት የለየናቸውን ጥቅሞች በማስታወስ ያነሳሱ
- ጊዜ ለይተው ድጋፋዊ ክትትል ያድርጉ