በቤት ለቤት ጉብኝት ወቅት መከናወን ያለባቸው ተግባራቶች
- የሚጎበኘውን ቤት በር ከመንካትዎ በፊት እና ጉብኝቱን እንዳጠናቀቁ እጅዎን በዉሃ እና ሳሙና ይታጠቡ ወይም በሳኒታይዘር ያጽዱ
- የቤት ጉብኝት ስታካሂዱ አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ (በመካከላችሁ 2 ሜትር መኖሩን አረጋግጡ)
- ሙቀት ለመለካትም ሆነ ታማሚ ለመለየት ሁሉም የቤተሰብ አባላት ወደ ደጅ ወይንም ውጭ እንዲዎጡ ይጠይቁ
- የፊትማስክ ያድርጉ
- በተቻለ መጠን የቤተሰብ አባላት በምርመራ ወቅት የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ/ማስክ እንዲለብሱ ምከሩ
- በቅኝትና አሠሣው ወቅት ሁሉንም የቤተሰብ አባላት ማግኘትዎን ያረጋግጡ (በምርመረው ወቅት ስላልተገኙ የቤተሰብ አባላት መቼ እንደሚገኙ መረጃ በመጠየቅ ዳግም ጉብኝት ያካሂዱ)
- ወላጆች ስለልጆቻቸው መረጃ መስጠት ይችላሉ ነገር ግን ልጆችን በአካል መመልከት አስፈላጊ ነው