የመተንፈሻ አካል ህመም የተገኘበት ሰው ቤት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

- የመተንፈሻ አካላት ህመም የተገኘበትን የቤተሰብ አባል አስፈላጊ መረጃ መሰብሰብና መመዝገብ
- በአቅራቢያዉ ለሚገኘዉ ጤና ጣቢያ ወዲያውኑ ማሳወቅና ማገናኘት
- ቁልፍ የኮቪድ 19 ቫይረስ መከላከያ ዘዴዎችን ለቤተሰብ አባላት ማስተላለፍ
- ምልክት ያሳየ/ች ወይም ያሳዩ የቤተሰብ አባል/ት እስኪጣራ ድረስ በቤት ውስጥ ለብቻ ተለይተዉ እንዲቆዩ ማድረግ
- የቤተሰብ አባላት በተቻለ መጠን የሚያስገድድ ሁኔታ ካልገጠማቸው ከቤት ባይወጡ ይመከራል
- የቤተሰብ አባላትን የአፍና አፍንጫ ማስክ/መሸፈኛ እንዲጠቀሙ መምከር
- ከማንኛዉም ንክኪ በኋላ እጆቻቸዉን በውሃና በሳሙና/አመድ ቢያንስ ከ40 እስከ 60 ሰከንድ እንዲታጠቡ ማስተማር
- ሲያስነጥሱ/ሲስሉ ሶፍት ወይም መሀረብ ይጠቀሙ ካልተቻለ ግን ክንዳቸው አጥፈዉ አፋቸዉን በመሸፈን እንዲስሉ/እንዲያስነጥሱ ማስተማር ከዚህ ዉጭ እጆቻቸዉ ላይ እንዳይጠቀሙ መምከር
- አካላዊ ርቀታቸውን አንዲጠብቁ ማስተማር
- ህመሙ ሊኖርባቸው ይችላል ተብሎ የተገመቱት ውጤታቸውን ከጤና ጣቢያዉመከታተልና መቀበል
- በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱን ማስተላለፍ እንደሚችሉ ያስገንዝቡ፡፡
9.6.1 የመተንፈሻ አካል ህመም ያልተገኘበት ሰው ቤት ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

- የመተንፈሻ አካል ህመም ልየታ ምርመራ የተደረገላቸውን ቤተሰብ አስፈላጊ መረጃዎችን መመዝገብ
- ቁልፍ የኮሮና ቫይረስ በሽታ የጤና መልዕክቶችን ለቤተሰብ አባላት አስተላልፉ፤
- የቤተሰብ አባላት በተቻለ መጠን የሚያስገድድ ሁኔታ ካልገጠማቸው ከቤት ባይወጡ ይመከራል
- የቤተሰብ አባላትን የአፍና አፍንጫ ማስክ/መሸፈኛ እንዲጠቀሙ መምከር
- ከማንኛዉም ንክኪ በኋላ እጆቻቸዉን በውሃና በሳሙና/አመድ ቢያንስ ከ40 እስከ 60 ሰከንድ እንዲታጠቡ ማስተማር
- ሲያስነጥሱ/ሲስሉ ሶፍት ወይም መሀረብ ይጠቀሙ ካልተቻለ ግን ክንዳቸው አጥፈዉ አፋቸዉን በመሸፈን እንዲስሉ/እንዲያስነጥሱ ማስተማር ከዚህ ዉጭ እጆቻቸዉ ላይ እንዳይጠቀሙ መምከር
- አካላዊ ርቀታቸውን አንዲጠብቁ ማስተማር
- የቤተሰብ አባል የመተንፈሻ አካላት ህመም (ጉንፋን) ምልክቶች ሲያሳዩ በማንኛውም ጊዜ የነጻ ስልክ ቁጥሮችን 8335፤ 952 ወይም የክልሎች ሌሎች የጥሪ አማራጮችን እንዲጠቀሙ መምከር
- በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ሳያሳዩ ቫይረሱን ማስተላለፍ እንደሚችሉ ያስገንዝቡ
9.6.2 ነፍሰ ጡር ያለበት ቤተሰብ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

- የቅድመ ወሊድ ክትትል አገልግሎት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሳይቋረጥ የሚሰጥ መሆኑን በማስገንዘብ ክትትላቸውን እንዲቀጥሉ ማበረታታት
- የቅድመ ወሊድ ክትትል አቋርጣ ከሆነ ወይም የገጠማት ችግር ካለ በመለየት በአቅራቢያ ከሚገኝ የጤና ተቋም ጋር ማገናኘት
- ለነፍሰጡር እናቶች በጤና ተቋማት የሚሰጡት አገልግሎቶች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማያደርግ ሁኔታ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መሆኑን ማስገንዘብ
9.6.3 ከ1 አመት በታች ህጻን ያለበት ቤተሰብ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

- መደበኛ የህጻናት ጤና አገልግሎት በሁሉም ጤና ተቋማት እየተሰጠ መሆኑን ማስገንዘብና አገልግሎቱን እንዲጠቀሙ ማድረግ
- የህጻናት ጤና ክትትል አቋርጠው ከሆነ ወይም የገጠማቸው ችግር ካለ ከጤና ተቋማት ጋር ማገናኘት
- በጤና ተቋማት የሚሰጡት የህጻናት ጤና አገልግሎቶች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማያደርግ ሁኔታ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ መሆኑን ማስገንዘብ
- ጡት የሚያጠቡ እናቶች በኮቪድ 19 በሽታ ቢያዙ ወይም ቢጠረጠሩ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ማጥባት እንደሚችሉ እና እንዳያቆሙ ማስተማር
9.6.4 ተላላፈ ያልሆኑ በሽታዎች ያላቸው ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ ውስጥ የሚከናወኑ ተግባራት

- ለቫይረሱ ሆነ በቫይረሱ ምክኒያት ለሚመጡ አደገኛ የጤና ችግሮች ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን እንዲረዱ በማድረግ በቤት ዉስጥ እንዲቆዩና ሌሎች ተገቢዉን ጥንቃቄዎች እንዲያደርጉ መምከር
- መደበኛ የህክምና እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች በጤና ተቋም ዉስጥ የኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭት መከላከል በሚያስችል ሁኔታ እየተሰጠ መሆኑን ማስገንዘብ
- ክትትል አቋርጠው ከሆነ ወይም የገጠማቸው ችግር ካለ ከጤና ተቋማት ጋር ማገናኘት