በስራ ቦታ ላይ ሊተላለፉ የሚገባቸዉን የኮቪድ 19 መከላከል ቁልፍ መልክቶች

- በስራ ቦታ ላይ ሊተላለፉ የሚገባቸዉን የኮቪድ 19 መከላከል ቁልፍ መልክቶችን አስተላልፉ
- ምልክት ያሳየ/ች ወይም ያሳዩ ሰራተኞች እስኪጣራ ድረስ ራሳቸውን በቤት ውስጥ እንዲያገሉና ንኪኪ እንዳይኖራቸው መምከር
- ሰራተኞችንና ተገልጋዮችን የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንዲጠቀሙ መምከር
- እጃቸውን ከማንኛዉም ንክኪ በኋላ በውሃና በሳሙና ከ40-60 ሰከንድ እንዲታጠቡ ወይም አልኮል ባልዉ እጅ ማጽጃ እንዲያጸዱ ማስተማር
- የስራ ቦታዉ በቂ የአየር ዝዉዉር እንዲኖር መምከር
- ሲያስነጥሱ/ሲስሉ በታጠፈ ክንድ ሸፍነው እንዲስሉ መንገር፤ አካላዊ ርቀታቸውን አንዲጠብቁ ማስተማር
- በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች የበሽታውን ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ ያስገንዝቡ
- ቆሻሻ በአግባቡ እንዲወገድ መምከር
- የታመመው ሰራተኛ/ደንበኛ በምርመራ በሽታው ያለበት መሆኑ ከተራጋገጠ ቅርርብ የነበራችው የስራ ባልደረቦች ስም ዝርዝር ለፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን (RRT - Rapid Response Team) ወይም ለጤና ጣቢያ ወዲያውኒ ማሳወቅና ማገናኘት
