የዘርፌ የመለማመጃ ታሪክ


ዘርፌ በቆሬ ቀበሌ የምትሰራ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ ናት። ዘርፌ የሁለት ልጆች እናት  ስትሆን ከቀበሌው አቅራቢያ በምትገኘው ከተማ ትኖራለች። የኮቨዲ-19 ዓለም ዐቀፍ ወረርሽኝ ሲከሰት የቀበሌው ማህበረሰብ ስለበሽታው ሁኔታ ለማወቅ ዘርፌን ያማክሯታል። ዘርፌ በየጊዜው የሚመጣውን የነዋሪ ጥያቄ አንድ በአንድ መመለስ ብቻ ሳይሆን እንደ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የሚጠበቅባትን ስራ መስራትም ጭምር ፍላጎት አድሮባታል። ከበሽታው  ጋር ተያይዞ የመጣው ፍርሀት በጤና ኬላዋ ያለው ክትትል መቀነስም አሳስቧታል።  ስለዘርፌ ከዚህ በመቀጠል የሚገኙትን ጥያቄዎች መልሱ